ሊኦፖልድ ሴዳር ሴንጎር
From Wikipedia
ሊኦፖልድ ሴዳር ሴንጎር (1906-2001) የሴኔጋል የመጀመሪያው መራሄ መንግስት በመሆን ከ1960 እስከ 1980 ድረስ ያገለገለ፣ ኔግሪቲዩድ የሚባለው ፍልስፍና ዋነኛ አቀንቃኝ የነበረ እና በግጥሞቹም አድናቆትን ያተረፈ አፍሪካዊ የሥነጽሁፍ ሰው ነው።
ሴንጎር የሴኔጋል ዋና ከተማ ከሆነችው ዳካር 70 ማይልስ ያህል በምትርቅ እና ጆአል ላ ፖርቱጊዝ (ጆአል ፖርቱጊዛዊቱዋ) በምትባል ትንሽ የአሳ አጥማጆች መንደር በ1906 ተወለደ። አባቱ ነጋዴ ከሆኑ ሴሬር ከሚባሉ ጎሳ የተወለደ ሲሆን እናቱ ግን ፔውል ከተባለ የሙስሊም ዘላን አርብቶአደሮች ጎሳ የተገኘች ነች። ሴንጎር ሁዋላ ላይ ሲጽፍ "ተወልጄ ያደኩት በአፍሪካ መኸል፣ የጎሳዎች እና ዘሮች መገናኛ ላይ ነው" ብሏል።
በ12 አመቱ የካቶሊክ ሚሲዮን ትምህርት ቤት ተመዝግቦ ትምህርቱን የጀመረ ሲሆን ከዛ በሁዋላ በሌሎች ትምህርት ቤቶችም በመማር በ1928 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን አጠናቁዋል። ከዚያም ፓሪስ ከሚገኘው ሊሴ ፓሪ ለግራንድ ከተባለው ትምህርት ቤት በ1931 ተመርቁዋል።